ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕዝራ 10:16-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጒዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤

17. በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡትን ወንዶች ሁሉ አጣርተው ጨረሱ።

18. ከካህናት ዘሮች መካከል ባዕዳን ሴቶችን ያገቡት ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፤ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ዘሮችና ከወንድሞቹ መካከል፤ መዕሤያ፣ አልዓዛር፣ ያሪብና ጎዶልያስ።

19. እነዚህ ሁሉ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ቃል በመግባት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም እያንዳንዳቸው ከመንጋው አንዳንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።

20. ከኢሜር ዘሮች፤አናኒና ዝባድያ።

21. ከካሪም ዘሮች፤መዕሤያ፣ ኤልያስ፣ ሸማያ፣ ይሒኤልና ዖዝያ።

22. ከፋስኩር ዘሮች፤ኤልዮዔናይ፣ መዕሤያ፣ ይስማኤል፣ ናትናኤል፣ ዮዛባትና ኤልዓሣ።

23. ከሌዋውያኑም መካከል፤ዮዛባት፣ ሰሜኢ፣ ቆሊጣስ የሚባል ቆልያ፣ ፈታያ፣ ይሁዳ፣ አልዓዛር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕዝራ 10