ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕዝራ 10:10-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ከዚያም ካህኑ ዕዝራ ተነሥቶ እንዲህ አላቸው፤ “እናንተ ታማኞች አልነበራችሁም፤ በእስራኤል በደል ላይ በደል በመጨመር ባዕዳን ሴቶችን አገባችሁ።

11. አሁንም ለአባቶቻችሁ አምላክ ለእግዚአብሔር ተናዘዙ፤ ፈቃዱን ፈጽሙ፤ በዙሪያችሁ ካሉት አሕዛብና ከባዕዳን ሚስቶቻችሁ ተለዩ።”

12. ጉባኤውም ሁሉ እንዲህ ሲሉ በታላቅ ድምፅ መለሱ፤ “እውነት ብለሃል፤ ያልኸውን መፈጸም ይገባናል።

13. ይሁን እንጂ በዚህ የተሰበሰበው ሕዝብ ብዙ ነው፤ ወቅቱም ክረምት ነው፤ ስለዚህ ውጭ መቆም አንችልም፤ ከዚህም በላይ በዚህ ነገር ብዙ ኀጢአት ስለ ሠራን፣ ይህ ጒዳይ በአንድና በሁለት ቀን የሚያልቅ አይደለም።

14. ስለዚህ ሹሞቻችን በማኅበሩ ሁሉ ምትክ መደረግ ያለበትን ያድርጉ። ከዚያም በዚህ የተነሣ የመጣው የአምላካችን ብርቱ ቊጣ ከእኛ እስኪመለስ ድረስ፣ በየከተሞቻችን ያሉ ባዕዳን ሴቶችን ያገቡ ሁሉ በየከተማው ካሉት ሽማግሌዎችና ዳኞች ጋር በተወሰነው ቀን ይምጡ።”

15. ይህንንም ነገር የተቃወሙት ከሜሱላምና ከሌዋዊው ከሳባታይ ድጋፍ ያገኙት የአሣሄል ልጅ ዮናታንና የቴቁዋ ልጅ የሕዝያ ብቻ ናቸው።

16. ስለዚህ ምርኮኞቹ እንደ ተባለው አደረጉ፤ ካህኑ ዕዝራም ከእያንዳንዱ የቤተ ሰብ ምድብ አንዳንድ የቤተ ሰብ ኀላፊ የሆነ ሰው መረጠ፤ ሁሉም በየስማቸው ተመዘገቡ። ከዚያም በዐሥረኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ጒዳዩን ለመመርመር ተቀመጡ፤

17. በመጀመሪያው ወር በመጀመሪያው ቀን ባዕዳን ሴቶችን ያገቡትን ወንዶች ሁሉ አጣርተው ጨረሱ።

18. ከካህናት ዘሮች መካከል ባዕዳን ሴቶችን ያገቡት ከዚህ የሚከተሉት ናቸው፤ከኢዮሴዴቅ ልጅ ከኢያሱ ዘሮችና ከወንድሞቹ መካከል፤ መዕሤያ፣ አልዓዛር፣ ያሪብና ጎዶልያስ።

19. እነዚህ ሁሉ ሚስቶቻቸውን ለመፍታት ቃል በመግባት እጃቸውን ሰጡ፤ ስለ በደላቸውም እያንዳንዳቸው ከመንጋው አንዳንድ አውራ በግ ለበደል መሥዋዕት አቀረቡ።

20. ከኢሜር ዘሮች፤አናኒና ዝባድያ።

21. ከካሪም ዘሮች፤መዕሤያ፣ ኤልያስ፣ ሸማያ፣ ይሒኤልና ዖዝያ።

22. ከፋስኩር ዘሮች፤ኤልዮዔናይ፣ መዕሤያ፣ ይስማኤል፣ ናትናኤል፣ ዮዛባትና ኤልዓሣ።

23. ከሌዋውያኑም መካከል፤ዮዛባት፣ ሰሜኢ፣ ቆሊጣስ የሚባል ቆልያ፣ ፈታያ፣ ይሁዳ፣ አልዓዛር።

24. ከመዘምራኑም መካከል፤ኤልያሴብ።ከበር ጠባቂቹም፣ሰሎም፣ ጤሌም፣ ኡሪ።

25. ከሌሎቹ እስራኤላውያን መካከል፤ከፋሮስ ዘሮች፤ ራምያ፣ ይዝያ፣ መልክያ፣ሚያሚን፣ አልዓዛር፣ መልክያና በናያስ።

26. ከኤላም ዘሮች፤መታንያ፣ ዘካርያስ፣ ይሒኤል፣ አብዲ፣ ይሬሞትና ኤልያ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕዝራ 10