ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕንባቆም 3:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ቀስትህን አዘጋጀህ፤ፍላጻም እንዲመጣልህ አዘዝህ፤ ሴላምድርን በወንዞች ከፈልህ፤

10. ተራሮች አዩህ፤ ተጨነቁም፤የውሃ ሞገድ ዐልፎ ሄደ፤ቀላዩ ደነፋ፤ማዕበሉንም ወደ ላይ አነሣ።

11. ከሚወረወሩ ፍላጾችህ፣ከሚያብረቀርቅ የጦርህ ነጸብራቅ የተነሣም፣ፀሓይና ጨረቃ በቦታቸው ቆሙ።

12. በምድር ላይ በመዓት ተመላለስህ፤ሕዝቦችንም በቊጣ ረገጥሃቸው።

13. ሕዝብህን ለመታደግ፣የቀባኸውንም ለማዳን ወጣህ፤የክፋትን ምድር መሪ ቀጠቀጥህ፤ከራስ ጠጒሩ እስከ እግር ጥፍሩም ዕርቃኑን አስቀረኸው። ሴላ

14. እንደ ዐውሎ ነፋስ ሊበታትነን የመጣውን፣ምስኪኑን በስውር በመዋጥ የሚደሰተውን፣የሰራዊት አለቃ ራስ፣በገዛ ጦሩ ወጋህ።

15. ታላላቅ ውሆችን በመናጥ፣ባሕሩን በፈረሶችህ ረገጥህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕንባቆም 3