ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕንባቆም 3:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. እግዚአብሔር ከቴማን፣ቅዱሱም ከፋራን ተራራ መጣ። ሴላክብሩ ሰማያትን ሸፈነ፤ውዳሴውም ምድርን ሞላ።

4. ጸዳሉ እንደ ፀሓይ ብርሃን ነው፤ጨረር ከእጁ ወጣ፤ኀይሉም በዚያ ተሰውሮአል።

5. መቅሠፍት በፊቱ ሄደ፤ቸነፈርም እግር በእግር ተከተለው።

6. ቆመ፤ ምድርን አንቀጠቀጠ፤ተመለከተ፤ ሕዝቦችን አብረከረከ፤የዘላለም ተራሮች ተፈረካከሱ፤የጥንት ኰረብቶችም ፈራረሱ፤መንገዱ ዘላለማዊ ነው።

7. የኢትዮጵያ ድንኳኖች ሲጨነቁ፣የምድያምም መኖሪያዎች ሲታወኩ አየሁ።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ በወንዞች ላይ ተቈጣህን?መዓትህስ በምንጮች ላይ ነበርን?በፈረሶችህና በድል አድራጊ ሠረገሎችህ፣በጋለብህ ጊዜ፣በባሕር ላይ ተቈጥተህ ነበርን?

9. ቀስትህን አዘጋጀህ፤ፍላጻም እንዲመጣልህ አዘዝህ፤ ሴላምድርን በወንዞች ከፈልህ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕንባቆም 3