ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዕንባቆም 2:17-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. በሊባኖስ ላይ የሠራኸው ግፍ ያጥለቀልቅሃል፤እንስሳቱን ማጥፋትህም ያስደነግጥሃል፤የሰው ደም አፍሰሃልና፤አገሮችንና ከተሞችን በውስጣቸው የሚኖሩትንም ሁሉ አጥፍተሃልና።

18. “የሰው እጅ የቀረጸው ጣዖት፣ሐሰትንም የሚናገር ምስል ምን ፋይዳ አለው?ሠሪው በገዛ እጁ ሥራ ይታመናልና፣መናገር የማይችሉ ጣዖታትን ይሠራልና።

19. ዕንጨቱን፣ ‘ንቃ!’ሕይወት የሌለውንም ድንጋይ፣ ‘ተነሣ!’ ለሚል ወዮለት፤በውኑ ማስተማር ይችላልን?እነሆ፤ በወርቅና በብር ተለብጦአል፤እስትንፋስም የለውም።

20. እግዚአብሔር ግን በተቀደሰ መቅደሱ አለ፣ምድር ሁሉ በፊቱ ጸጥ ትበል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዕንባቆም 2