ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 51:57-64 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

57. ባለ ሥልጣኖቿንና ጥበበኞቿን፣ገዦቿንና መኳንንቷን፣ ጦረኞቿንም አሰክራለሁ፤ለዘላለም ይተኛሉ፤ አይነቁምም፤”ይላል ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሥ።

58. የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ወፍራሙ የባቢሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈርሳል፤ከፍ ያሉት ደጆቿም በእሳት ይቃጠላሉ፤ሰዎቹ በከንቱ ይደክማሉ፤የሕዝቡም ልፋት ለእሳት ይሆናል።”

59. የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ የንጉሡ የግቢ አስከልካይ የነበረው የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ ከንጉሡ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ፣ ነቢዩ ኤርምያስ የሰጠው መልእክት ይህ ነው።

60. ኤርምያስ ስለ ባቢሎን ጽፎ ያስቀመጠውን ሁሉ፣ በባቢሎን ላይ የሚመጣውን ጥፋት ሁሉ በብራና ጥቅልል ላይ ጻፈው፤

61. ለሠራያም እንዲህ አለው፤ “ባቢሎን በደረስህ ጊዜ፣ ይህን ቃል ሁሉ ድምፅህን ከፍ አድርገህ ማንበብ አትዘንጋ

62. እንዲህም በል፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህችን ስፍራ ሰውም ሆነ እንስሳ እስከማይኖርባት ድረስ ለዘላለም ባድማ አደርጋታለሁ ብለሃል።’

63. ይህን ብራና አንብበህ ከጨረስህ በኋላ፣ ድንጋይ አስረህበት ኤፍራጥስ ወንዝ ውስጥ ጣለው፤

64. እንዲህም በል፤ ‘ባቢሎንም እኔ ከማመጣባት ጥፋት የተነሣ፣ እንደዚሁ ትሰጥማለች፤ ከእንግዲህም አትነሣም፤ ሕዝቧም ይወድቃል።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 51