ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 48:37-47 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

37. የእያንዳንዱ ሰው ራስ፣ጢምም ሁሉ ተላጭቶአል፤እጅ ሁሉ ተቸፍችፎአል፤ወገብም ሁሉ ማቅ ታጥቆአል።

38. በሞዓብ ቤቶች ጣራ ሁሉ ላይ፤፣በሕዝብም አደባባዮች፣ሐዘን እንጂ ሌላ የለም፤እንደማይፈለግ እንስራ፣ሞዓብን ሰብሬአለሁና፤”ይላል እግዚአብሔር።

39. “እንዴት ተንኰታኰተ! ምንኛስ አለቀሱ!ሞዓብ እንዴት ዐፍሮ ጀርባውን አዞረ!ሞዓብ የመሰደቢያ፣በዙሪያው ላሉትም ሁሉ የሽብር ምልክት ሆነ።”

40. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ እንደ ንስር ተወርውሮ ይወርድበታል፤ክንፎቹንም በሞዓብ ላይ ይዘረጋል።

41. ከተሞቹ ይወረራሉ፤ምሽጎቹም ይያዛሉ፤በዚያን ቀን የሞዓብ ጦረኞች ልብ፣በምጥ እንደ ተያዘች ሴት ልብ ይሆናል።

42. ሞዓብ እግዚአብሔርን አቃልሎአልና ይጠፋል፤መንግሥትነቱም ይቀራል።

43. የሞዓብ ሕዝብ ሆይ፤ሽብርና ጒድጓድ፣ ወጥመድም ይጠብቅሃል፤”ይላል እግዚአብሔር።

44. “ከሽብር የሚሸሽ ሁሉ፣ጒድጓድ ውስጥ ይገባል፤ከጒድጓዱም የሚወጣ፣በወጥመድ ይያዛል፤በሞዓብ ላይ፣የቅጣቱን ዓመት አመጣለሁና፣”ይላል እግዚአብሔር፤

45. “የሞዓብን ግንባር፣የደንፊዎችን ዐናት የሚያቃጥል፣እሳት ከሐሴቦን፣ነበልባል ከሴዎን ቤት ወጥቶአልና፤ኰብላዮች በሐሴቦን ጥላ ሥር፣ተስፋ ቈርጠው ቆመዋል።

46. ሞዓብ ሆይ፤ ወዮልህ!የካሞሽ ሕዝብ ተደምስሶአል፤ወንዶች ልጆችህ በምርኮ ተወስደዋል፤ሴቶች ልጆችህም ተግዘዋል።

47. “ነገር ግን የኋላ ኋላ፣የሞዓብን ምርኮ እመልሳለሁ፤”ይላል እግዚአብሔር።በሞዓብ ላይ የተወሰነው ፍርድ ይኸው ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 48