ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 48:27-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

27. በእስራኤል ላይ ስታላግጥ አልነበረምን?ስለ እርሷ በተናገርህ ቍጥር፣እያቃለልሃት ራስህን የምትነቀንቀውስ፣ከሌቦች ጋር ስትሰርቅ ተይዛለችን?

28. እናንተ በሞዓብ የምትኖሩ ሆይ፤ከከተማ ወጥታችሁ በዐለት መካከል ኑሩ፤በገደል አፋፍ ላይ ጐጆዋን እንደምትሠራ፣እንደ ርግብ ሁኑ።

29. “ስለ ሞዓብ ትዕቢት፣ስለ እብሪቱና ስለ ኵራቱ፣ስለ ትምክሕቱና ስለ መጓደዱ፣ስለ ልቡም ማበጥ ሰምተናል።

30. መዳፉን ዐውቃለሁ፤ ነገር ግን ከንቱ ነው፤”ይላል እግዚአብሔር።“ጒራውም ፋይዳ አይኖረውም።

31. ስለዚህ ለሞዓብ አለቅሳለሁ፤ለሞዓብ ምድር ሁሉ ዋይ እላለሁ፤ለቂርሔሬስ ሰዎችም የልቅሶ ድምፅ አሰማለሁ።

32. የሴባማ ወይን ሆይ፤ለኢያዜር ካለቀስሁት እንኳ ይልቅ አለቅስልሻለሁ፤ቅርንጫፎችሽ እስከ ባሕሩ ተዘርግተዋል፤እስከ ኢያዜርም ደርሰዋል፤ለመከር በደረሰው ፍሬሽና በወይንሽ ላይ፣አጥፊው መጥቶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 48