4. ፍልስጥኤማውያንን ሁሉ ለማጥፋት፣ተርፈውም የሚረዷቸውን ሁሉ፣ከጢሮስና ከሲዶና ለመቍረጥ፣ቀኑ ደርሶአልና። እግዚአብሔር በከፍቶር ዳርቻ የቀሩትን፣ ፍልስጥኤማውያንን ሊያጠፋተነሥቶአል።
5. ጋዛ በማዘን ራሷን ትላጫለች፣አስቀሎና አፏን ትይዛለች።በሜዳማ ስፍራ የምትገኙ ትሩፋን ሆይ፤እስከ መቼ ሰውነታችሁን ትቧጥጣላችሁ?
6. “ ‘የእግዚአብሔር ሰይፍ ሆይ፤የማታርፈው እስከ መቼ ነው?ወደ ሰገባህ ተመልሰህ ግባ፤ጸጥ ብለህ ተቀመጥ’ ትላላችሁ።
7. ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀሎናንና የባሕሩን ዳርቻ፣እንዲወጋ ሲያዝዘው፣እንዲፈጽመውም ትእዛዝ ሲሰጠው፣እንዴት ማረፍ ይችላል?”