ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 44:24-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ኤርምያስም ለሕዝቡና ለሴቶቹ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “በግብፅ የምትኖሩ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ።

25. የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ እናንተና ሚስቶቻችሁ፣ ‘ለሰማይዋ ንግሥት ለማጠንና የመጠጥ ቍርባን ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን’ ብላችሁ የገባችሁትን ቃል በተግባር አሳይታችኋል።’“እንግዲያውስ ወደ ኋላ አትበሉ፤ ቃል የገባችሁትን፤ ስእለታችሁንም ፈጽሙ።

26. በግብፅ የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል “ከእንግዲህ ወዲህ በየትኛውም የግብፅ ክፍል የሚኖር ማንኛውም አይሁዳዊ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብሎ ስሜን እንዳይጠራ፣ እንዳይምልም በታላቁ ስሜ ምያለሁ፤

27. ለመልካም ሳይሆን ለክፉ እተጋባቸዋለሁና፤ በግብፅ የሚኖሩ አይሁድ ፈጽሞ እስኪጠፉ ድረስ በሰይፍና በራብ ይደመሰሳሉ።

28. ከሰይፍ አምልጠው፣ ከግብፅ ወደ ይሁዳ ምድር የሚመለሱት በጣም ጥቂት ሰዎች ይሆናሉ። በግብፅ ምድር ለመኖር የመጡት የይሁዳ ቅሬታ ሁሉ፣ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማንኛችን ቃል እንደሚጸና ያውቃሉ።

29. “ ‘በእናንተ ላይ አመጣለሁ ያልሁትን ክፉ ነገር እንደሚፈጸም ታውቁ ዘንድ በዚህ ስፍራ እንደምቀጣችሁ ይህ ምልክት ይሁናችሁ’ ይላል እግዚአብሔር።

30. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን ሊገድለው ለፈለገው ጠላቱ ለባቢሎን ንጉሥ ለናቡከደናፆር አሳልፌ እንደ ሰጠሁ፣ እንዲሁ የግብፅን ንጉሥ ፈርዖን ሖፍራን ሊገድሉት ለሚፈልጉ ጠላቶቹ አሳልፌ እሰጠዋለሁ።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 44