ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 43:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኤርምያስ፣ እግዚአብሔር ለእነርሱ እንዲነግራቸው የላከውን የአምላካቸውን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ለሕዝቡ ተናግሮ በጨረሰ ጊዜ፣

2. የሆሽያ ልጅ ዓዛርያስ፣ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና ትዕቢተኞች የሆኑ ሰዎች ሁሉ ኤርምያስን እንዲህ አሉት፤ “ትዋሻለህ! አምላካችን እግዚአብሔር፣ ‘እዚያ ለመኖር ወደ ግብፅ አትሂዱ ብለህ ንገራቸው’ ብሎ አልላከህም፤

3. ነገር ግን ባቢሎናውያን እንዲገድሉን ወይም ማርከው ወደ ባቢሎን እንዲወስዱን ለእነርሱ አሳልፈህ ትሰጠን ዘንድ የኔርያ ልጅ ባሮክ በእኛ ላይ አነሣሥቶሃል።”

4. ስለዚህ የቃሬያ ልጅ ዮሐናንና፣ የጦር መኰንኖቹ ሁሉ እንዲሁም ሕዝቡ በሙሉ እግዚአብሔር በይሁዳ ምድር እንዲቀመጡ ያዘዛቸውን ቃል አልሰሙም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 43