ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 4:6-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ወደ ጽዮን ለመግባት ሰንደቅ ዐላማ አንሡ፤ቶሎ ሸሽታችሁ አምልጡ፤ከሰሜን መቅሠፍትን፣ታላቅ ጥፋትን አመጣለሁና።”

7. አንበሳ ከደኑ ወጥቶአል፤ሕዝብንም የሚያጠፋ ተሰማርቶአል፤ምድርሽን ባዶ ሊያደርግ፣ከስፍራው ወጥቶአል።ከተሞችሽ ፈራርሰው ይወድቃሉ፤ያለ ነዋሪም ይቀራሉ።

8. ስለዚህ ማቅ ልበሱ፤እዘኑ፤ ዋይ በሉ፤ የእግዚአብሔር አስፈሪ ቍጣ፣ከእኛ አልተመለሰምና።

9. ‘ “በዚያ ቀን” ይላል እግዚአብሔር፤“ንጉሡና ሹማምቱ ወኔ ይከዳቸዋል፤ካህናቱ ድንጋጤ ይውጣቸዋል፤ነቢያቱም ብርክ ይይዛቸዋል።”

10. እኔም፣ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰይፍ አንገታቸው ላይ ተቃጥቶ ሳለ፣ ‘ሰላም ይሆንላችኋል’ ብለህ ይህን ሕዝብና ኢየሩሳሌምን ለምን እጅግ አታለልህ?” አልሁ።

11. በዚያን ጊዜ፣ ለእዚህ ሕዝብና ለኢየሩሳሌም እንዲህ ተብሎ ይነገራል፤ “ለማበጠር ወይም ለማጥራት ሳይሆን፣ ከዚያ የበረታ የሚጠብስ ደረቅ ነፋስ በምድረ በዳ ካሉት ባድማ ኰረብቶች ወደ ወገኔ ሴት ልጅ

12. በእኔ ትእዛዝ ይነፍሳል፤ እንግዲህ ፍርዴን በእነርሱ ላይ እናገራለሁ።”

13. እነሆ፤ እንደ ደመና ይንሰራፋል፤ሠረገሎቹ እንደ ዐውሎ ነፋስ ይመጣሉ፤ፈረሶቹም ከንስር ይፈጥናሉ፤መጥፋታችን ነውና ወዮልን!

14. ኢየሩሳሌም ሆይ፤ እንድትድኚ ከልብሽ ክፋት ታጠቢ፤እስከ መቼ ክፉ ሐሳብ በውስጥሽ ይኖራል?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 4