ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 4:20-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ጥፋት በጥፋት ላይ ይመጣል፤ምድሪቱም በሞላ ባድማ ትሆናለች፤ድንኳኔ በድንገት፣መጠለያዬም በቅጽበት ጠፋ።

21. እስከ መቼ የጦርነት ዐርማ እመለከታለሁ?እስከ መቼስ የመለከት ድምፅ እሰማለሁ?

22. “ሕዝቤ ተላሎች ናቸው፤እኔን አያውቁኝም።ማስተዋል የጐደላቸው፣መረዳትም የማይችሉ ልጆች ናቸው።ክፋትን ለማድረግ ጥበበኞች፤መልካም መሥራት ግን የማያውቁ።”

23. ምድርን ተመለከትሁ፤እነሆ ቅርጽ የለሽና ባዶ ነበረች፤ሰማያትንም አየሁ፣ብርሃናቸው ጠፍቶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 4