ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 30:20-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ልጆቻቸው እንደ ቀድሞው ይሆናሉ፤ማኅበረ ሰቡም በፊቴ የጸና ይሆናል፤የሚጨቍኗቸውን ሁሉ እቀጣለሁ።

21. መሪያቸው ከራሳቸው ወገን ይሆናል፤ገዣቸውም ከመካከላቸው ይነሣል፤ወደ እኔ አቀርበዋለሁ፤ እርሱም ይቀርበኛል፤አለዚያማ ደፍሮ፣ወደ እኔ የሚቀርብ ማን ነው?ይላል እግዚአብሔር።

22. “ ‘ስለዚህ እናንተ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ፤እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።’ ”

23. እነሆ፣ የእግዚአብሔር ማዕበል፣በቍጣ ይነሣል፤የሚገለባብጥም ዐውሎ ነፋስ፣በክፉዎች ዐናት ላይ ይወርዳል።

24. የልቡን ሐሳብ ሳይፈጽም፣ የእግዚአብሔር ቍጣ፣እንዲሁ አይመለስም፤በሚመጡትም ዘመናት፣ይህን ታስተውላላችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 30