ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 3:22-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

22. “እናንት ከዳተኞች ልጆች ተመለሱ፤ከዳተኝነታችሁን እፈውሳለሁ።”“አንተ እግዚአብሔር አምላካችን ነህና፤አዎን፤ ወደ አንተ እንመጣለን።

23. በእርግጥ በኰረብቶች ላይ፣እንዲሁም በተራሮች ላይ፣ ሆ! ብለን መውጣታችን መታለል ነው፤በእርግጥ የእስራኤል መዳን፣በአምላካችን በእግዚአብሔር ነው።

24. ከለጋ ዕድሜአችን ጀምሮ፣የአባቶቻችንን የድካም ፍሬዎች፣በጎቻቸውንና ከብቶቻቸውን፣ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን፣ ነውረኛ ጣዖቶች በሏቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 3