ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 25:34-38 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. እናንት እረኞች፤ አልቅሱ፤ ዋይ በሉ፤እናንት የመንጋው ጌቶች፤ በዐመድ ላይ ተንከባለሉ፤የምትታረዱበት ቀን ደርሶአልና፤እንደ ውብ የሸክላ ዕቃ ወድቃችሁ ትከሰክሳላችሁ።

35. እረኞች የሚሸሹበት፣የመንጋ ጠባቂዎችም የሚያመልጡበት የለም።

36. እግዚአብሔር ማሰማሪያቸውን አጥፍቶአልና፣የእረኞችን ጩኸት፣የመንጋ ጠባቂዎችን ዋይታ ስሙ።

37. ከእግዚአብሔር ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣ሰላማዊው ምድር ባድማ ይሆናል።

38. እንደ አንበሳ ከጐሬው ይወጣል፤ከአስጨናቂው ሰይፍ፣ከቍጣውም የተነሣ፣ምድራቸው ባድማ ትሆናለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 25