ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 25:16-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. በጠጡም ጊዜ ይንገዳገዳሉ፤ በመካከላቸው ከምሰደው ሰይፍ የተነሣ ያብዳሉ።”

17. ስለዚህ ጽዋውን ከእግዚአብሔር እጅ ተቀብዬ እርሱ ወደ ላከኝ ሕዝቦች ሁሉ ሄድሁ፤ እንዲጠጡትም አደረግሁ፤

18. ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ባድማና ሰዎች የሚጸየፉአቸው መዘባበቻና ርግማን እንዲሆኑ፦ ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች፣ ነገሥታቷንና ባለሥልጣኖቿን፣

19. የግብፅን ንጉሥ ፈርዖንን፣ አገልጋዮቹን፣ ባለሥልጣኖቹንና ሕዝቡን ሁሉ፣

20. በዚያ የሚኖሩትን ድብልቅ ሕዝብ ሁሉ፣ የዖፅ ምድር ነገሥታትን ሁሉ፣ በአስቀሎና፣ በጋዛ፣ በአቃሮንና በአዛጦንም ሕዝብ ቅሬታ ያሉትን የፍልስጥኤም ነገሥታት፣

21. ኤዶምን፣ ሞዓብን፣ አሞንን፣

22. የጢሮስንና የሲዶናን ነገሥታት ሁሉ፣ ከባሕሩ ማዶ ያሉ የጠረፍ ምድር ነገሥታትን፣

23. ድዳንን፣ ቴማንን፣ ቡዝን፣ ጠጒራቸውን ዙሪያውን የሚከረከሙትን ሕዝብ ሁሉ፣

24. የዐረብ ነገሥታትን ሁሉ፣ በምድረ በዳ የሚኖሩትን የድብልቅ ሕዝብ ነገሥታት ሁሉ፣

25. የዘምሪ፣ የኤላምና የሜዶን ነገሥታትን ሁሉ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 25