ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 2:30-36 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

30. “ልጆቻችሁን በከንቱ ቀጣኋቸው፤እነርሱም አልታረሙም።ሰይፋችሁ እንደ ተራበ አንበሳ፣ነቢያታችሁን በልቶአል።

31. “የዚህ ትውልድ ሰዎች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል አስተውሉ፤“እኔ ለእስራኤል ሕዝብ ምድረ በዳ፣ወይስ ድቅድቅ ጨለማ ያለበት ምድር ሆንሁበትን?ሕዝቤ፣ እንደ ልባችን ልንሆን እንፈልጋለን፤ተመልሰንም ወደ አንተ አንመጣም’ ለምን ይላል?

32. ለመሆኑ ቆንጆ ጌጣጌጧን፣ሙሽራ የሰርግ ልብሷን ትረሳለችን?ሕዝቤ ግን፣እጅግ ብዙ ቀን ረስቶኛል።

33. በፍትወት ለማጥመድ እንዴት ስልጡን ነሽ?ልክስክስ ክፉ ሴቶች እንኳ ከመንገድሽ ብዙ ክፋት ይማራሉ።

34. በስርቆት ያልያዝሻቸው፣የንጹሓን ድኾች ደም፣በልብስሽ ላይ ተገኝቶአል።ይህን ሁሉ አድርገሽም፣

35. ‘እኔ ንጹሕ ነኝ፤በእርግጥ ቍጣው ከእኔ ርቆአል’ ትያለሽ።እኔ ግን እፈርድብሻለሁ፤‘ኀጢአት አልሠራሁም ብለሻልና።

36. መንገድሽን እየለዋወጥሽ፣ለምን ትሮጫለሽ?አሦር እንዳዋረደሽ፣ግብፅም እንዲሁ ያዋርድሻል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 2