ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፤

2. “ሂድና ጮኸህ ይህን ለኢየሩሳሌም ጆሮ አሰማ፤“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤‘በወጣትነትሽ ጊዜ የነበረሽን ታማኝነት፣በሙሽርነትሽም ወራት እንዴት እንደ ወደድሽኝ፣በምድረ በዳ ዘር በማይዘራበት ምድር፣እንዴት እንደተከተልሽኝ አስታውሳለሁ።

3. እስራኤል ለእግዚአብሔር ቅዱስ ነበረች፤የመከሩም በኵር ነበረች፤የዋጧት ሁሉ በደለኞች ሆኑ፤መዓትም ደረሰባቸው’ ”ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 2