ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 16:14-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. “ስለዚህ ሰዎች፦ ‘እስራኤላውያንን ከግብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው ከእንግዲህ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል” ይላል እግዚአብሔር፤

15. “ነገር ግን፣ እስራኤላውያንን ከሰሜን ምድርና እነርሱን ከበተነባቸው ከሌሎች አገሮች ሁሉ ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!’ ይላሉ፤ ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠኋቸው ምድር እመልሳቸዋለሁና።

16. “አሁን ግን ብዙ ዓሣ አጥማጆችን እልካለሁ” ይላል እግዚአብሔር፤ “እነርሱም ያጠም ዷቸዋል። ከዚያም በኋላ ብዙ አዳኞችን እሰዳለሁ፤ እነርሱም ከየተራራው፣ ከየኰረብታው ሁሉ ከየዐለቱም ስንጣቂ አድነው ይይዟቸዋል።

17. ዐይኔ በመንገዳቸው ሁሉ ላይ ነው፤ በፊቴ የተገለጡ ናቸው፤ ኀጢአታቸውም ከዐይኔ የተሰወረ አይደለም።

18. ምድሬን በድን በሆኑ አስጸያፊ ጣዖቶቻቸው ስላረከሱ፣ ርስቴንም በአሳፋሪ ነገሮች ስለሞሉ፣ ላደረጉት በደልና ኀጢአት ዕጥፍ እከፍላቸዋለሁ።”

19. ብርታቴና ምሽጌ፣በመከራ ቀን መጠጊያዬ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤አሕዛብ ከምድር ዳርቻ፣ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤“አባቶቻችን ለአንዳች ነገር ያልረቧቸውን ከንቱ ጣዖቶች፣የሐሰት አማልክትን ወረሱ።

20. ሰዎች ለራሳቸው አማልክትን ያበጃሉን?ያደርጉ ይሆናል፤ እንዲህ ዐይነቶቹ ግን አማልክት አይደሉም።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 16