ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 15:12-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. “ሰው ብረትን፣ ከሰሜን የመጣን ብረት፣ነሐስንስ መስበር ይችላልን?

13. በመላ አገርህ፣ስላለው ኀጢአትህ ሁሉ፣ሀብትና ንብረትህን፣ያለ ዋጋ አሳልፌ ለምርኮ እሰጣለሁ።

14. ቍጣዬ በላያችሁ፣የሚነድ እሳት ትጭራለችና፣በማታውቀው አገር፣ለጠላቶችህ ባሪያ አደርግሃለሁ።”

15. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ታውቃለህ፤እንግዲህ አስበኝ፤ ጐብኘኝም፤አሳዳጆቼን ተበቀልልኝ።ታጋሽ እንደ መሆንህ አታጥፋኝ፤ባንተ ምክንያት የሚደርስብኝን ነቀፋ አስብ።

16. ቃልህ በተገኘ ጊዜ በላሁት፤የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤በስምህ ተጠርቻለሁና፣ቃልህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆነልኝ።

17. ፈንጠዝያ ከሚያደርጉት ጋር አልተቀመጥሁም፤ከእነርሱም ጋር አልፈነጨሁም፤እጅህ በላዬ ስለ ነበር፣ በቍጣህ ስለ ሞላኸኝ፣ለብቻዬ ተቀመጥሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 15