ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 13:24-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. “የበረሓ ነፋስ ብትንትኑን እንደሚያወጣው ገለባ፣እንዲሁ እበታትናችኋለሁ።

25. እኔን ረስተሽ፣በከንቱ አማልክት ስለታመንሽ፣ያወጅሁልሽ ድርሻሽ፣ዕጣ ፈንታሽ ይህ ነው፤”ይላል እግዚአብሔር፤

26. “ኀፍረትሽ እንዲገለጥ፣ልብስሽን ፊትሽ ድረስ እገልባለሁ፤

27. በኰረብቶችና በሜዳዎች ላይ፣አስጸያፊ፣ ተግባርሽን፣ምንዝርናሽንና ማሽካካትሽን፣ኀፍረተቢስ ግልሙትናሽን አይቻለሁ።ኢየሩሳሌም ሆይ፤ ወዮልሽ፤ከርኵሰትሽ የማትጸጂው እስከ መቼ ነው?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 13