ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 12:8-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ርስቴ፣ በዱር እንዳለ አንበሳተነሥታብኛለችበእኔም ላይ ጮኻብኛለች፤ስለዚህ ጠላኋት።

9. ርስቴ ሌሎች አሞሮች፣ሊበሏት እንደ ከበቧት፣እንደ ዝንጒርጒር አሞራ አልሆነችምን?ሂዱ፤ የዱር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፤እንዲቀራመቷትም አምጧቸው።

10. ብዙ እረኞች የወይን ቦታዬን ያጠፋሉ፤ይዞታዬንም ይረግጣሉ፤ደስ የምሰኝበትንም ማሳ፣ጭር ያለ በረሓ ያደርጉታል።

11. በፊቴ ባድማ፣ደረቅና ወና ይሆናል፤መላዪቱም ምድር ጠፍ ትሆናለች፤ስለ እርሷ የሚገደው የለምና።

12. በምድረ በዳ ባሉት ወና ኰረብቶች ላይ፣አጥፊዎች ይሰማራሉ፤ የእግዚአብሔር ሰይፍ ከምድር ጫፍ እስከ ምድር ጫፍ፣አንዳች ሳያስቀር ይበላል፤የሚተርፍም የለም።

13. ስንዴን ይዘራሉ፤ እሾኽን ያጭዳሉ፤ይደክማሉ፤ የሚያገኙት ግን የለም፤ ከእግዚአብሔርም ጽኑ ቍጣ የተነሣ፣በመኸራችሁ ውጤት ታፍራላችሁ።”

14. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ለሕዝቤ ለእስራኤል የሰጠሁትን ርስት የሚይዙትን ክፉ ጎረቤቶቼን ሁሉ፣ ከምድራቸው እነቅላቸዋለሁ፤ የይሁዳንም ቤት ከመካከላቸው እነቅላለሁ፤

15. ከነቀልኋቸው በኋላ ግን መልሼ እምራቸዋለሁ፤ እያንዳንዳቸውንም ወደ ገዛ አገራቸውና ወደ ገዛ ርስታቸው መልሼ አመጣቸዋለሁ፤

16. የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩና ሕዝቤን በበኣል እንዲምል እንዳስ ተማሩት ሁሉ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው በስሜ ቢምሉ፣ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ፤

17. የማይሰማኝን ሕዝብ ግን ፈጽሜ እነቅለዋለሁ፤ አጠፋዋለሁም” ይላል እግዚአብሔር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 12