ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 12:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. “ቤቴን እተዋለሁ፤ርስቴን እጥላለሁ፤የምወዳትን እርሷን፣አሳልፌ በጠላቶቿ እጅ እሰጣታለሁ።

8. ርስቴ፣ በዱር እንዳለ አንበሳተነሥታብኛለችበእኔም ላይ ጮኻብኛለች፤ስለዚህ ጠላኋት።

9. ርስቴ ሌሎች አሞሮች፣ሊበሏት እንደ ከበቧት፣እንደ ዝንጒርጒር አሞራ አልሆነችምን?ሂዱ፤ የዱር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፤እንዲቀራመቷትም አምጧቸው።

10. ብዙ እረኞች የወይን ቦታዬን ያጠፋሉ፤ይዞታዬንም ይረግጣሉ፤ደስ የምሰኝበትንም ማሳ፣ጭር ያለ በረሓ ያደርጉታል።

11. በፊቴ ባድማ፣ደረቅና ወና ይሆናል፤መላዪቱም ምድር ጠፍ ትሆናለች፤ስለ እርሷ የሚገደው የለምና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 12