ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኤርምያስ 11:19-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት ነበርሁ፤ እነርሱም፣“ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ፤ከሕያዋን ምድር እናጥፋው፤ከእንግዲህም ወዲያ ስሙ አይታሰብ።”ብለው እንዳደሙብኝ ዐላወቅሁም ነበር።

20. ልብንና ኵላሊትን የምትመረምር፣በጽድቅም የምትፈርድ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ጒዳዬን ላንተ ትቻለሁና፤በእነርሱ ላይ የምትፈጽመውን በቀል ልይ።

21. “እንግዲህ ሕይወትህን ለማጥፋት ለሚሹና፣ ‘በእግዚአብሔር ስም ትንቢት አትናገር፤ አለዚያ በእጃችን ትሞታለህ’ ለሚሉህ ለዓናቶት ሰዎች እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤

22. ስለዚህ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ እኔ እቀጣቸዋለሁ፤ ጐልማሶቻቸው በሰይፍ፣ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውም በራብ ይሞታሉ።

23. በሚቀጡበት ዓመት በዓናቶት ሰዎች ላይ መዓት ስለማመጣ፣ ከእነርሱ የሚተርፍ አንድም አይኖርም።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኤርምያስ 11