ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 9:5-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ሳያውቁት፣ ተራሮችን ይነቅላቸዋል፤በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።

6. ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤ምሰሶዎቿንም ያንቀጠቅጣል።

7. ፀሓይን ያዛታል፤ አትወጣምም፤ከዋክብትንም በማኅተም ያሽጋል።

8. እርሱ ብቻውን ሰማያትን ዘርግቶአል፤በባሕርም ማዕበል ላይ ይራመዳል።

9. እርሱ የድብና የኦሪዮን፣የፕልያዲስና የደቡብ ከዋክብት ፈጣሪ ነው፤

10. የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮችን፣የማይቈጠሩ ታምራትንም ያደርጋል።

11. እነሆ! በአጠገቤ ሲያልፍ አላየውም፤በጐኔም ሲሄድ፣ ልገነዘበው አልችልም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 9