ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 9:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. መዓት ወርዶ ድንገት ሰው ሲጨርስ፣በንጹሓን መከራ ይሣለቃል።

24. ምድር በክፉዎች እጅ ስትወድቅ፣እርሱ የፈራጆቿን ዐይን ይሸፍናል፤ታዲያ፣ ይህን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል?

25. “ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፣አንዳችም ደስታ ሳያይ ያልፋል።

26. ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ፣ለመንጠቅ ቍልቍል እንደሚበር ንስር ይፈጥናል።

27. ‘ማጒረምረሜን እረሳለሁ፤ገጽታዬን ቀይሬ ፈገግ እላለሁ’ ብል፣

28. ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 9