ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 9:21-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. “ያለ ነቀፋ ብሆንም እንኳ፣ስለ ራሴ ግድ የለኝም፤የገዛ ሕይወቴንም እንቃታለሁ።

22. ሁሉም አንድ ነው፤‘እርሱ ጻድቁንና ኀጥኡን ያጠፋል’ የምለውም ለዚህ ነው።

23. መዓት ወርዶ ድንገት ሰው ሲጨርስ፣በንጹሓን መከራ ይሣለቃል።

24. ምድር በክፉዎች እጅ ስትወድቅ፣እርሱ የፈራጆቿን ዐይን ይሸፍናል፤ታዲያ፣ ይህን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ማን ሊሆን ይችላል?

25. “ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፣አንዳችም ደስታ ሳያይ ያልፋል።

26. ከደንገል እንደ ተሠራ ታንኳ፣ለመንጠቅ ቍልቍል እንደሚበር ንስር ይፈጥናል።

27. ‘ማጒረምረሜን እረሳለሁ፤ገጽታዬን ቀይሬ ፈገግ እላለሁ’ ብል፣

28. ንጹሕ አድርገህ እንደማትቈጥረኝ ስለማውቅ፣መከራዬን ሁሉ እፈራለሁ።

29. በደለኛ መሆኔ ካልቀረ፣ለምን በከንቱ እለፋለሁ?

30. ሰውነቴን በሳሙና ብታጠብ፣እጄንም በልዩ መታጠቢያ ባነጻ፣

31. ልብሴ እንኳ እስኪጸየፈኝ ድረስ፣በዐዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ።

32. “መልስ እሰጠው ዘንድ፣ እሟገተውም ዘንድ፣እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም።

33. በሁለታችን ላይ እጅ የሚጭን፣በመካከላችንም የሚዳኝ ቢኖር፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 9