ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 9:2-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. “በእርግጥ ነገሩ እንዲህ እንደሆነ ዐውቃለሁ፤ነገር ግን ሥጋ ለባሽ በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ጻድቅ ሊሆን ይችላል?

3. ሰው ከእርሱ ጋር ለመከራከር ቢፈልግ፤ከሺህ ጥያቄ እንዱን እንኳ መመለስ አይችልም።

4. ጥበቡ ጥልቅ፣ ኀይሉም ታላቅ ነውና፤እርሱን ተቃውሞ ያለ አንዳች ጒዳት የሄደ ማን ነው?

5. ሳያውቁት፣ ተራሮችን ይነቅላቸዋል፤በቍጣውም ይገለብጣቸዋል።

6. ምድርን ከስፍራዋ ያናውጣታል፤ምሰሶዎቿንም ያንቀጠቅጣል።

7. ፀሓይን ያዛታል፤ አትወጣምም፤ከዋክብትንም በማኅተም ያሽጋል።

8. እርሱ ብቻውን ሰማያትን ዘርግቶአል፤በባሕርም ማዕበል ላይ ይራመዳል።

9. እርሱ የድብና የኦሪዮን፣የፕልያዲስና የደቡብ ከዋክብት ፈጣሪ ነው፤

10. የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮችን፣የማይቈጠሩ ታምራትንም ያደርጋል።

11. እነሆ! በአጠገቤ ሲያልፍ አላየውም፤በጐኔም ሲሄድ፣ ልገነዘበው አልችልም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 9