ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 9:12-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ቢነጥቅ፣ ማን ይከለክለዋል?‘ምን መሥራትህ ነው?’ የሚለውስ፣ ማን ነው?

13. እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ረዓብን የሚረዱ እንኳ ይሰግዱለታል።

14. “ታዲያ፣ ከእርሱ ጋር እሟገት ዘንድ፣ልከራከረውም ቃላት እመርጥ ዘንድ፣ እንዴት እችላለሁ?

15. ጻድቅ ብሆንም እንኳ፣ ልመልስለት አልችልም፤ዳኛዬን ምሕረት ከመለመን ሌላ ላደርግ የምችለው የለም።

16. ጠርቼው ‘አቤት!’ ቢለኝም፣ያዳምጠኛል ብዬ አላምንም።

17. በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፤ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል፤

18. ምሬትን አጠገበኝ እንጂ፣ለመተንፈስ እንኳ ፋታ አልሰጠኝም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 9