ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 8:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ድሩ ላይ ቢደገፍ፣ ይበጠስበታል፤አጥብቆም ቢይዘው አይጸናም።

16. ውሃ እንደ ጠገበ ተክል፣ ፀሓይ እየሞቀው፣ቅርንጫፉን ሁሉ በአትክልቱ ስፍራ ላይ ይዘረጋል።

17. ሥሩን በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጥማል፤በዐለትም መካከል ስፍራ ያበጃል።

18. ከስፍራው ሲወገድ ግን፣ያ ቦታ ‘አይቼህ አላውቅም’ ብሎ ይክደዋል።

19. እነሆ፤ ሕይወቱ በዚህ ያከትማል፤ሌሎች አትክልትም ከመሬት ይበቅላሉ።

20. “እነሆ፤ እግዚአብሔር እንከን የሌለበትን ሰው አይጥልም፤የክፉዎችንም እጅ አያበረታም፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 8