ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 8:11-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ደንገል ረግረግ በሌለበት ስፍራ ይበቅላልን?ቄጠማስ ውሃ በሌለበት ይለመልማልን?

12. ገና በማደግ ላይ እያለ ሳይታጨድ፣ከሌሎች ዕፀዋት ፈጥኖ ይደርቃል።

13. እግዚአብሔርን የሚረሱ መጨረሻቸው እንዲህ ነው፤አምላክ የለሽ ኑሮ የሚኖሩም ሁሉ ተስፋቸው ትጠፋለች።

14. መተማመኛው ቀጭን ክር፣ድጋፉም የሸረሪት ድር ነው።

15. ድሩ ላይ ቢደገፍ፣ ይበጠስበታል፤አጥብቆም ቢይዘው አይጸናም።

16. ውሃ እንደ ጠገበ ተክል፣ ፀሓይ እየሞቀው፣ቅርንጫፉን ሁሉ በአትክልቱ ስፍራ ላይ ይዘረጋል።

17. ሥሩን በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጥማል፤በዐለትም መካከል ስፍራ ያበጃል።

18. ከስፍራው ሲወገድ ግን፣ያ ቦታ ‘አይቼህ አላውቅም’ ብሎ ይክደዋል።

19. እነሆ፤ ሕይወቱ በዚህ ያከትማል፤ሌሎች አትክልትም ከመሬት ይበቅላሉ።

20. “እነሆ፤ እግዚአብሔር እንከን የሌለበትን ሰው አይጥልም፤የክፉዎችንም እጅ አያበረታም፤

21. እንደ ገና አፍህን በሣቅ፤ከንፈሮችህንም በእልልታ ይሞላል።

22. ጠላቶችህ ኀፍረት ይለብሳሉ፤የክፉዎችም ድንኳን ይጠፋል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 8