ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 8:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሹሐዊውም በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “እንዲህ ያለውን ነገር የምትናገረው፣ቃልህም እንደ ብርቱ ነፋስ የሚሆነው እስከ መቼ ነው?

3. እግዚአብሔር ፍትሕን ያጣምማልን?ሁሉን ቻይ አምላክስ ጽድቅን ያጣምማልን?

4. ልጆችህ በእርሱ ላይ ኀጢአት ሠርተው ከሆነ፣ለኀጢአታቸው ቅጣት አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።

5. ነገር ግን አንተ ወደ እግዚአብሔር ብትመለከት፣ሁሉን ቻይ አምላክን ብትማፀን፣

6. ንጹሕና ቅን ብትሆን፣ እርሱ ስለ አንተ አሁኑኑ ይነሣል፤ወደ ተገቢውም ስፍራህ ይመልስሃል።

7. ጅማሬህ አነስተኛ ቢመስልም፣ፍጻሜህ እጅግ ታላቅ ይሆናል።

8. “የቀደመውን ትውልድ ጠይቅ፤አባቶቻቸውም የደረሱበትን መርምረህ አግኝ፤

9. እኛ ትናንት ስለ ተወለድን አንዳች አናውቅምና፤ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው።

10. እነርሱ የሚያስተምሩህና የሚነግሩህ፣ከልቦናቸውም ቃልን የሚያወጡ አይደሉምን?

11. ደንገል ረግረግ በሌለበት ስፍራ ይበቅላልን?ቄጠማስ ውሃ በሌለበት ይለመልማልን?

12. ገና በማደግ ላይ እያለ ሳይታጨድ፣ከሌሎች ዕፀዋት ፈጥኖ ይደርቃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 8