ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 6:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤

17. በበጋ ወራት ግን ይጠፋል፤በሙቀትም ጊዜ መፋሰሻው ላይ አይገኝም።

18. ሲራራ ነጋዴዎች ውሃ አጥተው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፤ወደ በረሓም ገብተው ይጠፋሉ።

19. የቴማን ነጋዴዎች ውሃ ይፈልጋሉየሳባ መንገደኞችም ተስፋ ያደርጋሉ፤

20. እርግጠኞች ሆነው ስለ ነበር ተሰቀቁ፤እዚያ ደረሱ፣ ግን ዐፈሩ።

21. አሁንም እናንተ እንደዚያ ሆናችሁብኝ፣መከራዬን አይታችሁ ፈራችሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 6