ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 6:14-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. “ለወዳጁ በጎነት የማያሳይ ሰው፣ሁሉን የሚችለውን አምላክ መፍራት ትቶአል።

15. ወንድሞቼ ግን እንደማያዛልቅ ጅረት፣ለጊዜው ሞልቶ እንደሚፈስ ወንዝ የማይታመኑ ናቸው፤

16. በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤

17. በበጋ ወራት ግን ይጠፋል፤በሙቀትም ጊዜ መፋሰሻው ላይ አይገኝም።

18. ሲራራ ነጋዴዎች ውሃ አጥተው መንገዳቸውን ይቀይራሉ፤ወደ በረሓም ገብተው ይጠፋሉ።

19. የቴማን ነጋዴዎች ውሃ ይፈልጋሉየሳባ መንገደኞችም ተስፋ ያደርጋሉ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 6