ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 6:13-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ያልተሳካልኝ ሰው ነኝና፣ራሴን ለመርዳት ምን ጒልበት አለኝ?

14. “ለወዳጁ በጎነት የማያሳይ ሰው፣ሁሉን የሚችለውን አምላክ መፍራት ትቶአል።

15. ወንድሞቼ ግን እንደማያዛልቅ ጅረት፣ለጊዜው ሞልቶ እንደሚፈስ ወንዝ የማይታመኑ ናቸው፤

16. በረዶ በሟሟ ጊዜ ወንዙ ይደፈርሳል፤ዐመዳይም በቀለጠ ጊዜ ይሞላል፤

17. በበጋ ወራት ግን ይጠፋል፤በሙቀትም ጊዜ መፋሰሻው ላይ አይገኝም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 6