ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 6:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤

2. “ምነው ሐዘኔ በተመዘነ!መከራዬም ሚዛን ላይ በተቀመጠ!

3. ከባሕር አሸዋ ይልቅ በከበደ፣ኀይለ ቃሌም ባላስገረመ ነበር!

4. ሁሉን የሚችል አምላክ ፍላጻ በውስጤ ነው፤መንፈሴም መርዙን ትጠጣለች፤የእግዚአብሔር ማስደንገጥ ተሰልፎብኛል።

5. የሜዳ አህያ ሣር እያለው፣በሬስ ድርቆሽ እያለው፣ ይጮኻልን?

6. የማይጣፍጥ ምግብ ያለ ጨው ይበላልን?ወይስ የዕንቍላል ውሃ ጣዕም አለውን?

7. እንዲህ ዐይነቱን ምግብ እጸየፋለሁ፤ለመንካትም አልፈልግም።

8. “ምነው ልመናዬ በተመለሰልኝ፤እግዚአብሔር የምመኘውን በሰጠኝ፤

9. እግዚአብሔር አድቅቆ ያጠፋኝ ዘንድ፣ምነው እጁ በተፈታ!

10. ፋታ በማይሰጥ ሕመም ውስጥ እየተደሰትሁ፣ይህ መጽናኛ በሆነልኝ ነበር፤የቅዱሱን ትእዛዝ አልጣስሁምና።

11. “አሁንም ተስፋ አደርግ ዘንድ ብርታቴ፣እታገሥስ ዘንድ አለኝታዬ ምንድን ነው?

12. የድንጋይ ጒልበት አለኝን?ሥጋዬስ ናስ ነውን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 6