ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 5:4-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ልጆቹ የኑሮ ዋስትና የራቃቸው፤በፍርድ አደባባይ ጥቃት የደረሰባቸው፣ ታዳጊ የሌላቸው ናቸው።

5. ከእሾህ መካከል እንኳ አውጥቶ፤ራብተኛ ሰብሉን ይበላበታል፤ጥማተኛም ሀብቱን ይመኝበታል።

6. ችግር ከምድር አይፈልቅም፤መከራም ከመሬት አይበቅልም።

7. ፍንጣሪው ከእሳቱ ላይ ሽቅብ እንደሚወረወር፣ሰውም ለመከራ ይወለዳል።

8. “እኔ ብሆን ኖሮ፣ ወደ እግዚአብሔር በቀረብሁ፣ጒዳዬንም በፊቱ በገለጽሁለት ነበር።

9. እርሱ፣ የማይመረመሩ ድንቅ ነገሮች፣የማይቈጠሩም ታምራት ያደርጋል።

10. ምድሪቱን በዝናብ ያረሰርሳል፤ሜዳውንም ውሃ ያጠጣል።

11. የተዋረዱትን በከፍታ ቦታ ያስቀምጣል፤ያዘኑትንም ወደ አስተማማኝ ስፍራ ያወጣቸዋል።

12. እጃቸው ያሰቡትን እንዳይፈጽም፣የተንኰለኞችን ዕቅድ ያከሽፋል።

13. ጠቢባንን በጥበባቸው ይይዛል፤የተንኰለኞችንም ሤራ ያጠፋል።

14. ቀኑ ጨለማ ይሆንባቸዋል፤በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳለ ሰው በዳበሳ ይሄዳሉ።

15. ችግረኛውን ከአፋቸው ሰይፍ፣ከኀይለኛውም እጅ ያድነዋል።

16. ስለዚህ ድኻ ተስፋ አለው፤ዐመፅም አፏን ትዘጋለች።

17. “እነሆ፤ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው፤ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ተግሣጽ አትናቅ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 5