ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 5:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “እስቲ ተጣራ፤ የሚመልስልህ አለን?ከቅዱሳንስ ወደ ማንኛው ዘወር ትላለህ?

2. ሞኙን ሰው ብስጭት ይገድለዋል፤ቂሉንም ቅናት ያጠፋዋል።

3. ቂል ሰው ሥር ሰዶ አየሁት፤ግን ድንገት ቤቱ ተረገመ።

4. ልጆቹ የኑሮ ዋስትና የራቃቸው፤በፍርድ አደባባይ ጥቃት የደረሰባቸው፣ ታዳጊ የሌላቸው ናቸው።

5. ከእሾህ መካከል እንኳ አውጥቶ፤ራብተኛ ሰብሉን ይበላበታል፤ጥማተኛም ሀብቱን ይመኝበታል።

6. ችግር ከምድር አይፈልቅም፤መከራም ከመሬት አይበቅልም።

7. ፍንጣሪው ከእሳቱ ላይ ሽቅብ እንደሚወረወር፣ሰውም ለመከራ ይወለዳል።

8. “እኔ ብሆን ኖሮ፣ ወደ እግዚአብሔር በቀረብሁ፣ጒዳዬንም በፊቱ በገለጽሁለት ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 5