ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 42:5-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ጆሮዬ ስለ አንተ ሰምታ ነበር፤አሁን ግን ዐይኔ አየችህ።

6. ስለዚህ ራሴን እንቃለሁ፤በትቢያና በዐመድ ላይ ተቀምጬ ንስሓ እገባለሁ።”

7. እግዚአብሔር ይህን ለኢዮብ ከተናገረ በኋላ፣ ቴማናዊውን ኤልፋዝን እንዲህ አለው፤ “እንደ አገልጋዬ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ቅን ነገር ስላልተናገራችሁ፣ ቍጣዬ በአንተና በሁለቱ ባልንጀሮችህ ላይ ነዶአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 42