ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 41:25-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. እርሱ በተነሣ ጊዜ፣ ኀያላን ይርዳሉ፤በሚንቀሳቀስበትም ጊዜ ወደ ኋላ ያፈገፍጋሉ።

26. ጦር፣ ፍላጻ ወይም አንካሴ፣ሰይፍም ቢያገኘው አንዳች አይጐዳውም።

27. እርሱ ብረትን እንደ አገዳ፣ናስንም እንደ ነቀዘ ዕንጨት ይቈጥራል።

28. ቀስት አያባርረውም፤የወንጭፍ ድንጋይም ለእርሱ እንደ ገለባ ነው።

29. ቈመጥ በእርሱ ፊት እንደ ገለባ ነው፤ጦር ሲሰበቅ ይሥቃል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 41