ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 36:5-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. “እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው።

6. ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል።

7. ዐይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሣም፤ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ለዘላለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።

8. ነገር ግን ሰዎች በሰንሰለት ቢታሰሩ፣በመከራም ገመድ ቢጠፈሩ፣

9. በእብሪት የፈጸሙትን በደል፣ተግባራቸውን ይነግራቸዋል።

10. ተግሣጽን እንዲሰሙ ያደርጋቸዋል፤ከክፋታቸውም እንዲመለሱ ያዛቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 36