ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 36:24-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣የእርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ።

25. ሰው ሁሉ አይቶታል፤ሰዎችም በትኵረት ተመልክተውታል።

26. እነሆ፤ እግዚአብሔር ከአእምሯችን በላይ ታላቅ ነው!የዘመኑም ቍጥር ከመታወቅ ያልፋል።

27. “የውሃን ነጠብጣብ ወደ ላይ ያተናል፤መልሶም በዝናብ መልክ በጅረቶች ላይ ያወርዳል፤

28. ደመናት ጠል ያንጠባጥባሉ፤ዶፍም በሰው ላይ ይወርዳል።

29. ደመናትን እንዴት እንደሚዘረጋ፣ከድንኳኑም እንዴት እንደሚያንጐደጒድ ሊረዳ የሚችል ማን ነው?

30. መብረቁን በዙሪያው እንዴት እንደሚበትን ተመልከት፤የባሕሩንም ወለል ይሸፍናል።

31. እርሱ ሕዝብን የሚያስተዳድረው፣ ምግብንም አትረፍርፎ የሚሰጣቸውበዚህ መንገድ ነው።

32. እጆቹን በመብረቅ ይሞላቸዋል፤ዒላማውንም እንዲመታ ያዝዘዋል።

33. ነጐድጓዱ ውሽንፍር እንደሚከተለው ያመለክታል፤ከብቶችም እንኳ መምጣቱን ይጠቍማሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 36