ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 36:14-25 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. በቤተ ጣዖት ውስጥ ዝሙት በሚፈጽሙት መካከል፣ገና በወጣትነታቸው ይቀጫሉ።

15. ነገር ግን የሚሠቃዩትን ከሥቃያቸው ያድናቸዋል፤በመከራቸውም ውስጥ ይናገራቸዋል።

16. “አንተንም ከመከራ መንጋጋ፣ጭንቀት ወደሌለበት ወደ ሰፊ ስፍራ፣ምርጥ ምግብ ወደ ሞላበት ማእድ ያወጣሃል።

17. አሁን ግን ለክፉዎች የሚገባው ፍርድ በላይህ ተጭኖአል፤ፍርድና ብይን ይዘውሃል።

18. ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።

19. ባለጠግነትህም ሆነ ብርቱ ጥረትህ ሁሉ፣ችግር ውስጥ እንዳትገባ ሊረዳህ ይችላልን?

20. ሰዎች ከቤታቸው የሚወሰዱበትን፣ሌሊት አትመኝ።

21. ከመከራ ይልቅ መርጠኸዋልና፣ወደ ክፋት እንዳትመለስ ተጠንቀቅ።

22. “እነሆ፤ እግዚአብሔር በኀይሉ ከፍ ከፍ ብሎአል፤እንደ እርሱስ ያለ አስተማሪ ማን ነው?

23. እርሱን መንገድ የሚመራው፣ወይም ‘ይህን አጥፍተሃል’ የሚለው ማን ነው?

24. ሰዎች በመዝሙር ያወደሱትን፣የእርሱን ሥራ ማወደስ አትዘንጋ።

25. ሰው ሁሉ አይቶታል፤ሰዎችም በትኵረት ተመልክተውታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 36