ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 36:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኤሊሁ በመቀጠል እንዲህ አለ፤

2. “በእግዚአብሔር ፈንታ ሆኜ የምለው አለኝ፤ጥቂት ታገሠኝና እነግርሃለሁ።

3. ዕውቀቴን ከሩቅ አመጣለሁ፤ፈጣሪዬ ጻድቅ እንደሆነ እገልጻለሁ።

4. ቃሌ ሐሰት እንዳልሆነ አረጋግጣለሁ፤በዕውቀቱ ፍጹም የሆነ ሰው ከአንተ ጋር ነው።

5. “እግዚአብሔር ኀያል ነው፤ ግን ማንንም አይንቅም፤ኀያል፣ በዐላማውም ጽኑ ነው።

6. ክፉዎችን በሕይወት አያኖርም፤ለተቸገሩት ግን በቅን ይፈርዳል።

7. ዐይኖቹን ከጻድቃን ላይ አያነሣም፤ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፤ለዘላለምም ከፍ ከፍ ያደርጋቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 36