ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 32:13-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ‘እኛ ጥበብ አግኝተናል፤ሰው ሳይሆን እግዚአብሔር ይርታው’ አትበሉ።

14. ኢዮብ ግን ቃሉን በእኔ ላይ አልሰነዘረም፤እኔም እንደ እናንተ አነጋገር መልስ አልሰጠውም።

15. “እነርሱ ተስፋ ቈርጠው፤ የሚሉት የላቸውም፤የሚናገሩትም ጠፍቶአቸዋል።

16. እንግዲህ እነርሱ መልስ ስላጡ፣ጸጥ ብለውም ስለ ቆሙ፣ በትዕግሥት ልጠብቅን?

17. እኔም የምለው ይኖረኛል፤የማውቀውንም እገልጣለሁ።

18. የምናገረው ሞልቶኛልና፤በውስጤ ያለውም መንፈስ ገፋፍቶኛል።

19. ውስጤ እንደ ተከደነና መተንፈሻ እንዳጣ የወይን ጠጅ፣ሊፈነዳ እንደ ተቃረበም አዲስ የወይን ጠጅ አቁማዳ ሆኖአል።

20. ተናግሬ መተንፈስ አለብኝ፤አፌንም ከፍቼ መልስ መስጠት ይገባኛል።

21. ለማንም አላደላም፤ሰውንም አላቈላምጥም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 32