ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 31:36-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

36. በእርግጥ ትከሻዬ ላይ በደረብሁት፣እንደ አክሊልም ራሴ ላይ በደፋሁት ነበር።

37. እያንዳንዱን ርምጃዬን በገለጽሁለት፣እንደ ልዑል እየተንጐራደድሁ በቀረብሁት ነበር።

38. “ዕርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ ከሆነ፣ትልሞቿ ሁሉ በእንባ ርሰው እንደሆነ፣

39. ፍሬዋን ያለ ዋጋ በልቼ፣የባለመሬቶቿን ነፍስ አሳዝኜ ከሆነ፣

40. በስንዴ ፈንታ እሾህ፣በገብስም ምትክ ዐረም ይብቀልብኝ።”የኢዮብ ቃል ተፈጸመ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 31