ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 31:29-40 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. “በጠላቴ ውድቀት ደስ ብሎኝ፣በደረሰበትም መከራ ሐሤት አድርጌ እንደሆነ፣

30. እኔ ግን በነፍሱ ላይ ክፉ እንዲመጣ በመራገም፣አንደበቴን ለኀጢአት ከቶ አሳልፌ አልሰጠሁም።

31. የቤቴ ሰዎች፣ ‘ከኢዮብ ከብት ሥጋ አስቈርጦ፣ያልጠገበ ማን ነው’ ብለው ካልሆነ፣

32. ነገር ግን ቤቴ ለመንገደኛው ዘወትር ክፍት ስለ ነበር፣መጻተኛው በጐዳና ላይ አያድርም ነበር።

33. ሰዎች እንደሚያደርጉት በደሌን በልቤ በመሰወር፤ኀጢአቴን ሸሽጌ ከሆነ፣

34. ሕዝቡን በመፍራት፣የወገኖቼንም ንቀት በመሸሽ፣ወደ ደጅ ሳልወጣ፣ ዝም ብዬ ቤት ውስጥ አልተቀመጥሁም።

35. “ምነው የሚሰማኝ ባገኝ!የመከላከያ ፊርማዬ እነሆ፤ ሁሉን የሚችል አምላክ ይመልስልኝ፤ከሳሼም ክሱን በጽሑፍ ያቅርብ።

36. በእርግጥ ትከሻዬ ላይ በደረብሁት፣እንደ አክሊልም ራሴ ላይ በደፋሁት ነበር።

37. እያንዳንዱን ርምጃዬን በገለጽሁለት፣እንደ ልዑል እየተንጐራደድሁ በቀረብሁት ነበር።

38. “ዕርሻዬ በእኔ ላይ ጮኻ ከሆነ፣ትልሞቿ ሁሉ በእንባ ርሰው እንደሆነ፣

39. ፍሬዋን ያለ ዋጋ በልቼ፣የባለመሬቶቿን ነፍስ አሳዝኜ ከሆነ፣

40. በስንዴ ፈንታ እሾህ፣በገብስም ምትክ ዐረም ይብቀልብኝ።”የኢዮብ ቃል ተፈጸመ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 31