ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 31:23-33 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. የእግዚአብሔርን ቍጣ በመፍራቴ፣እንዲህ ያሉ ነገሮች መፈጸም አልቻልሁም።

24. “ወርቅን ተስፋ አድርጌ፣ወይም ንጹሑን ወርቅ፣ ‘አንተ መታመኛዬ ነህ’ ብዬ ከሆነ፣

25. እጄ ባገኘችው ሀብት፣በባለጠግነቴም ብዛት ደስ ብሎኝ ከሆነ፣

26. የፀሓይን ድምቀት አይቼ፣ወይም የጨረቃን አካሄድ ግርማ ተመልክቼ፣

27. ልቤ በስውር ተታልሎ፣ስለ ክብራቸው አፌ እጄን ስሞ ከሆነ፣

28. ለልዑል እግዚአብሔር ታማኝ አለመሆኔ ነውና፣ይህም ደግሞ የሚያስቀጣኝ በደል በሆነ ነበር።

29. “በጠላቴ ውድቀት ደስ ብሎኝ፣በደረሰበትም መከራ ሐሤት አድርጌ እንደሆነ፣

30. እኔ ግን በነፍሱ ላይ ክፉ እንዲመጣ በመራገም፣አንደበቴን ለኀጢአት ከቶ አሳልፌ አልሰጠሁም።

31. የቤቴ ሰዎች፣ ‘ከኢዮብ ከብት ሥጋ አስቈርጦ፣ያልጠገበ ማን ነው’ ብለው ካልሆነ፣

32. ነገር ግን ቤቴ ለመንገደኛው ዘወትር ክፍት ስለ ነበር፣መጻተኛው በጐዳና ላይ አያድርም ነበር።

33. ሰዎች እንደሚያደርጉት በደሌን በልቤ በመሰወር፤ኀጢአቴን ሸሽጌ ከሆነ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 31