ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ኢዮብ 31:16-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. “ለድኻ የሚያስፈልገውን ከልክዬ ከሆነ፣ወይም የመበለቲቱን ዐይን አፍዝዤ ከሆነ፣

17. እንጀራዬን ከድኻ አደጉ ጋር ሳልካፈል፣ለብቻዬ በልቼ ከሆነ፣

18. ይልቁን ድኻ አደጉን ከታናሽነቴ ጀምሮ እንደ አባት አሳደግሁት፤መበለቲቱንም ከተወለድሁ ጀምሮ መንገድ መራኋት፤

19. በልብስ ዕጦት ሰው ሲጠፋ፣ወይም ዕርቃኑን ያልሸፈነ ድኻ አይቼ፣

20. በበጎቼ ጠጒር ስላሞቅሁት፣ልቡ ባርኮኝ ካልሆነ፣

21. በአደባባይ ተሰሚነት አለኝ ብዬ፣በድኻ አደጉ ላይ እጄን አንሥቼ ከሆነ፣

22. ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይነቀል፤ክንዴም ከመታጠፊያው ይሰበር፤

23. የእግዚአብሔርን ቍጣ በመፍራቴ፣እንዲህ ያሉ ነገሮች መፈጸም አልቻልሁም።

24. “ወርቅን ተስፋ አድርጌ፣ወይም ንጹሑን ወርቅ፣ ‘አንተ መታመኛዬ ነህ’ ብዬ ከሆነ፣

25. እጄ ባገኘችው ሀብት፣በባለጠግነቴም ብዛት ደስ ብሎኝ ከሆነ፣

26. የፀሓይን ድምቀት አይቼ፣ወይም የጨረቃን አካሄድ ግርማ ተመልክቼ፣

27. ልቤ በስውር ተታልሎ፣ስለ ክብራቸው አፌ እጄን ስሞ ከሆነ፣

28. ለልዑል እግዚአብሔር ታማኝ አለመሆኔ ነውና፣ይህም ደግሞ የሚያስቀጣኝ በደል በሆነ ነበር።

29. “በጠላቴ ውድቀት ደስ ብሎኝ፣በደረሰበትም መከራ ሐሤት አድርጌ እንደሆነ፣

30. እኔ ግን በነፍሱ ላይ ክፉ እንዲመጣ በመራገም፣አንደበቴን ለኀጢአት ከቶ አሳልፌ አልሰጠሁም።

31. የቤቴ ሰዎች፣ ‘ከኢዮብ ከብት ሥጋ አስቈርጦ፣ያልጠገበ ማን ነው’ ብለው ካልሆነ፣

32. ነገር ግን ቤቴ ለመንገደኛው ዘወትር ክፍት ስለ ነበር፣መጻተኛው በጐዳና ላይ አያድርም ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ኢዮብ 31